የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ። Ethiopians' Citizen Democratic Union | Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens የመርበቢያ ፡ አድራሻ ፤ www.slttunhzb.net የእ-ጦማር ፡ አድራሻ ፤ sh1@ttomar.net ________________________________ ገ_ዐዓ_201701_ዐማርኛ የኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ የ2017 ፡ ዓ.ም. ፡ መልካም ፡ ምኞት ፡ መልእክት ፡ ለኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፦ « የመሸጋገሪያ ፡ ዘመን ፡ ይኹንልን ! » የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ሆይ ! የኢትዮጵያ ፡ አምላክ ፥ እግዚአብሔር ፥ እንኳን ፡ ለ2017 ፡ ዓ.ም. ፡ በደኅና ፡ አደረሰኽ ፡ እያለ ፡ ውጥን ፡ አካልኽ ፡ የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ፡ ( ኢ.ሀ.ሥ.አ. ) ፡ ላዲሱ ፡ ዓመት ፡ የድል ፣ የአንድነት ፣ የነጻነት ፡ እና ፡ የሰላም ፡ ምኞቱን ፡ በፍጹም ፡ ትሕትና ፡ ያቀርብልኻል ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ሆይ ! በ1966 ፡ ዓ.ም. ፡ በኢትዮጵያ ፡ የደረሰውን ፡ የመንግሥታዊ ፡ ሥርዐት ፡ ለውጥ ፡ 51ኛ ፡ ዓመት ፡ ዘንድሮ ፡ ስናስታውስ ፥ እስከዚህች ፡ ዕለት ፡ ድረስ ፡ ውድ ፡ ሀገራችን ፡ ኢትዮጵያ ፡ በውንብድና ፡ አገዛዝ ፡ መዳፍ ፡ ሥር ፡ መማቀቋንም ፡ በሐዘን ፡ እናስባለን ። በዚህ ፡ ዅሉ ፡ ዘመን ፥ የኢትዮጵያ ፡ ስያሳዊ ፡ ኹኔታ ፡ በደም ፡ ዐበላ ፡ ደፍርሶ ፡ መኖሩን ፡ " በፍጹም ፡ አልቀበልም ! በቃኝ ! " ብለኽ ፥ አንተ ፡ የኢትዮጵያ ፡ ነጻ ፡ ሕዝብ ፡ ዐምሐራ ፥ ከጥቂት ፡ ዓመት ፡ ወዲህ ፡ በፋኖ፟ነት ፡ ተደራጅተኽ ፡ በመዋጋትኽ ፡ እና ፡ ተፈላጊውን ፡ መሥዋዕትነት ፡ በመክፈልኽ ፥ እንሆ ፥ የመከራኽ ፡ እና ፡ የደም ፡ መፋሰስኽ ፡ ዋና ፡ ምክንያት ፡ የኾነውን ፡ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ን ፡ እና ፡ ሕገ ፡ ውንብድናውን ፡ ከእነግብር ፡ ዐበሮቹ ፡ ገርስሰኽ ፡ ልትጥላቸው ፡ ተቃርበኻል ። የትግልኽ ፡ መነሻም ፡ መድረሻም ፡ የሀገራዊ ፡ እግዚእናኽ ፡ መከበር ፡ ስለ ፡ ኾነ ፥ ከግራም ፡ ከቀኝም ፡ መንገድ ፡ ሊያስቱኽ ፡ የሚጐነታትሉኽን ፡ በትዕግሥት ፡ እና ፡ በዘዴ ፥ ሲያስፈልግም ፡ በኀይል ፡ እየመከትክ ፡ ዐልፈኽ ፥ የመሸጋገሪያ ፡ መንግሥትኽን ፡ በመመሥረት ፡ እና ፡ በዐዲስ ፡ ሕገ ፡ መንግሥት ፡ ዘላቂውን ፡ መንግሥትኽን ፡ በመከወን ፡ ሀገራዊ ፡ እግዚእናኽን ፡ አስከብረኽ ፡ ዐላማኽን ፡ ትፈጽመዋለኽ ፡ ሲል ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ሙሉ ፡ እምነቱን ፡ ይገልጽልኻል ። በትግሉ ፡ አመራር ፡ ረገድ ፥ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ያቀረበልኽም ፦ "ሥልጡንሕዝባዊ ፡ የመሸጋገሪያ ፡ መንግሥት ፡ ሀገራዊ ፡ ቅያስ ። " ( www.slttunhzb.net ) በሕዝብ ፡ ዘንድ ፡ እና ፡ በፋኖ፟ ፡ መሪዎች ፡ ዘንድ ፡ ሰፊ ፡ ተቀባይነትን ፡ በማግኘቱ ፥ ዅሉንም ፡ ከልብ ፡ እያመሰገነ ፥ ኀይላችንን ፡ በማዋሐድ ፡ 2017 ፡ ዓ.ም.ን ፡ የድል ፡ ዓመት ፡ ልናደርገው ፡ እንደምንችል ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ሙሉ ፡ እምነቱን ፡ በድጋሚ ፡ ይገልጽልኻል ፨ ትሑት ፡ አገልጋይኽ ፥ ኢ.ሀ.ሥ.አ.