የኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ዜና ፡ መግለጫ ፡ (2014-01-26 ፡ ዓ.ም.) | E.C.D.U. PRESS RELEASE (2021-10-26)| COMMUNIQUÉ DE PRESSE DE L'U.C.D.E. (2021-10-26) የኢትዮጵያውያን   ፡ ሀገራዊ   ፡ ሥልጡንሕዝባዊ   ፡ አንድነት   ። Ethiopians' Citizen Democratic Union | Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens www.slttunhzb.net sh1@ttomar.net _______ ዜመ_ኢ-1_20140126_ዐማርኛ ዜና ፡ መግለጫ ። የሙት ፡ ይዘት ፡ ትድገት ፧ በባዕድ ፡ ሠራሽ ፡ ሕገ ፡ ወጥ ፡ "ሕገ ፡ መንግሥት" ፡ መሠረት ፡ የቆመው ፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ⁽1⁾ ፡ ቅሬታ ፡ ይዘት ⁽2⁾ ፥ በግብዝ ፡ ምርጫ ፡ የሥልጣን ፡ ተገቢነትን ፡ ሊያገኝ ፡ አይችልም ። _______ ለንደን ፥ መስከረም ፡ 26 ፡ ቀን ፡ 2014 ፡ ዓ.ም. ። ከሠኔ ፡ 14 ፡ ቀን ፡ 2013 ፡ ዓ.ም. ፡ አንሥቶ ፡ በኢትዮጵያ ፡ የተካኼደው ፡ ግብዝ ፡ ምርጫ፦ • የኢትዮጵያን ፡ ሕዝብ ፡ አንድነት ፡ እና ፡ እግዚእና ፡ በካደ ፣ • የአፓርትሀይድ ፡ ሥርዐትን ፡ በሀገር ፡ ላይ ፡ በተከለ ፣ • ሀገር ፡ ኢትዮጵያን ፡ ባለቤት ፡ አልባ ፡ አስቀርቶ ፡ ለብዝበዛ ፡ በሚዳርግ ፣ ሕገ ፡ ወጥ ፣ ንኅለተኛ ፡ ("ኒኂሊስት") ፡ እና ፡ ባዕድ ፡ ሠራሽ ፡ "ሕገ ፡ መንግሥት" ፡ መሠረት ፥ በሕገ ፡ ወጥ ፡ አገዛዝ ፡ የተጠራ ፡ በመኾኑ ፥ ውጤቱ ፡ አስቀድሞ ፡ ፉርሽና ፡ ውድቅ ፡ ኾኗል ፤ ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቀሬታ ፡ ይዘትም ፡ የተመኘውን ፡ የሥልጣን ፡ ተገቢነት ፡ አያስገኝለት ፥ የተያያዘውንም ፡ የፍርሰት ፡ ኺደት ፡ አይቀለብስለት ፡ ሲል ፥ የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ፡ (ኢ.ሀ.ሥ.አ.) ፡ ለኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ እና ፡ ለዓለም ፡ መንግሥታት ፡ ያስታውቃል ። መስከረም ፡ 26 ፡ ቀን ፡ 2014 ፡ ዓ.ም. ፡ ይቋቋማል ፡ የተባለውም ፡ "ዐዲስ ፡ መንግሥት" ፥ የሕ.ወ.ሐ.ት.ን ⁽3⁾ ፡ ዐናት ፡ ቈርጦ ፡ ከመቀነሱ ፡ በቀር ፥ ላለፉት ፡ 30 ፡ ዓመታት ፡ በንጹሓን ፡ ደም ፡ የታጠበውና ፡ በሙስና ፡ ነቀርሳ ፡ የተደወየው ፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቅሬታ ፡ አካል ፡ ስለ ፡ ኾነ ፥ የማፋረስ ፡ አንዳች ፡ ተስፋ ፡ የለውም ። ፋሺስቱን ፡ ሕ.ወ.ሐ.ት. ፡ በኢትዮጵያ ፡ "የምዕራባዊ ፡ ምልክዮሽ ፡ ተላላኪ" ፡ ብሎ ፡ በመሥዋዕት ፡ በግነት ፡ የሚያቀርብ ፥ ጕራጁን ፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቀሬታ ፡ ይዘት ፡ ደግሞ ፡ "ብቻውን ፡ ለኢትዮጵያ ፡ የቆመ" ፡ ብሎ ፡ የሚያቀርብ ፥ የምዕራባውያን ፡ ኀይሎችን ፡ ቡራኬና ፡ ሙሉ ፡ ተሳትፎ ፡ ያገኘ ፥ ሕዝብን ፡ የማሞኘትና ፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ የሙት ፡ ይዘትን ፡ የመታደግ ፡ አስተዛዛቢ ፡ ዘዴ ፥ እንሆ ፥ ላለፉት ፡ ወራት ፡ ሲከናወን ፡ ከርሟል ። ምርጫው ፡ ከመካኼዱ ፡ ጥቂት ፡ ወራት ፡ አንሥቶ ፥ የይዘቱን ፡ የጡት ፡ አባት ፡ የተባበሩት ፡ የአሜሪካ ፡ ኹነቶችን ፡ ጨምሮ ፥ አንድ ፡ አንድ ፡ የምዕራብ ፡ መንግሥታት ፥ ልዩ ፡ ልዩ ፡ ምክንያቶችን ፡ አስታከው ፡ ባወጧቸው ፡ ይፋ ፡ መግለጫዎቻቸው ፥ ማወራኛዎቻቸው ፡ ደግሞ ፡ አግንነው ፡ በተለየ ፡ ግህደት ፡ ባስተጋቡላቸው ፡ "ፀረ ፡ ኢትዮጵያ" ፡ አቋሞቻቸው ፥ ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቀሬታ ፡ ይዘት ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ ድጋፍ ፡ ሞልቶ ፡ እንዲገ፟ኝለት ፡ የተቀነባበረ ፡ ተንኰል ፡ ተፈጽሟል ። ከነዚህ ፡ ድርጊቶች ፡ ውስጥ ፡ በተለይ ፡ የሚጠቀሰው ፡ በወቅቱ ፡ የአሜሪካው ፡ ርእሰ ፡ ሀገር ፡ ዶናልድ ፡ ትራምፕ ፡  / Donald Trump ፡ በቀጥታ ፡ በሚተላለፍ ፡ የኑኀ ፡ ርእየት ፡ ("ቴሌቪዥን") ፡ ዝግጅት ፡ ላይ ፥ ኢትዮጵያ ፡ በጥቍር ፡ አባ፟ይ ፡ ወንዝ ፡ ላይ ፡ የምትገነባውን ፡ ግድብ ፡ የግብጽ ፡ መንግሥት ፡ እንዲያፈነዳው ፡ ለግብጹ ፡ ርእሰ ፡ ሀገር ፡ ዤኔራል ፡ ኧልሲሲ ፡ የሰጡት ፡ "ኀላፊነት ፡ የጐደለው" ፡ ሐሳብ ፡ ይገኝበታል ። የተፍገመገመው ፡ የሱዳን ፡ የሽግግር ፡ መንግሥትም ፡ የኢትዮጵያን ፡ ድንበር ፡ በመጣስና ፡ ብሔሯን ፡ በመውረር ፣ ሰላማውያንንና ፡ ወታደሮችን ፡ የገደለበት ፣ ንብረትንም ፡ ያጠፋበትና ፡ የዘረፈበት ፥ ሌላው ፡ ግድያን ፡ የጨመረ ፡ የውክልና ፡ ጥቃት ፡ ነው ። እነዚህ ፡ የሚያስነውሩ ፡ ድርጊቶች ፡ ዅሉ ፡ የምዕራባውያን ፡ መንግሥታቱን ፡ የውጭ ፡ ስያስ ፡ (የውጭ ፡ "ፖሊሲ") ፡ በዓለም ፡ ኅብረተሰብ ፡ ፊት ፡ አላስከበረላቸውም ። በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቀሬታ ፡ ይዘት ፡ የሥልጣን ፡ አልቦነትም ፡ ረገድ ፥ ሙከራቸው ፡ ምንም ፡ የሚለውጠው ፡ ነገር ፡ አይኖርም ። እንዲያውም ፡ የባሰውን ፥ እነዚህ ፡ የውጭ ፡ ኀይሎች ፡ በኢትዮጵያ ፡ ለንጹሓን ፡ ሕይወት ፡ በከንቱ ፡ መጥፋት ፡ በቀጥታም ፡ ኾነ ፡ በተዘዋዋሪ ፡ መንገድ ፡ እጃቸው ፡ እንዳለበት ፡ አሳይቷል ። ይህን ፡ በኢትዮጵያ ፡ የውስጥ ፡ ጕዳይ ፡ ጣልቃ ፡ የመግባት ፡ ሕገ ፡ ወጥ ፡ ድርጊታቸውን ፡ የኢትዮጵያውያን ፡ ሀገራዊ ፡ ሥልጡንሕዝባዊ ፡ አንድነት ፡ (ኢ.ሀ.ሥ.አ.) ፡ በጥብቅ ፡ ያወግዛል ። በ"ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.-ብልጽግና ፡ ፓርቲ-ሸኔ" ፡ የሚ፟መ፟ራ፟ው ፡ መንደር ፡ ገነን ፡ አገዛዝ ፥ ላለፉት ፡ ሦስት ፡ ዓመታት፦ • መላ፟ ፡ ሀገሪቱን ፡ የመበታተንን ፣ • ለፀረ ፡ ሀገራዊ / ፀረ ፡ ዐምሐራ ⁽4⁾ ፡ ዐላማው ፡ በሚልዮን ፡ የሚቈጠሩ ፡ ንጹሓንን ፡ የማስፈጀትንና ፡ የማፈናቀልን ፣ • ተቀናቃኞቹን ፡ የማሰር ፡ ወይም ፡ የመግደል ፣ • የሀገርን ፡ ሀብትና ፡ የሕዝብን ፡ ርስት ፡ ለውጭ ፡ ኀይሎች ፡ የመቸብቸብንና ፡ ሌሎች ፡ ወንጀሎችንም ፥ በገሃድ ፣ አላንዳች ፡ ስወራ ፣ በማናለ፟ብኝነት ፡ ሲፈጽማቸው ፡ ቈይቷል ። በግንቦት ፡ ወር ፡ 2013 ፡ ዓ.ም. ፥ መንደር ፡ ገነኑ ፡ አገዛዝ ፥ በሌለው ፡ ሥልጣን ፥ የኢትዮጵያን ፡ የአንከርት ፡ ስልክ ፡ ሀገራዊ ፡ ገበያ ፡ ከፍሎ ፡ በብሪታንያዊው ፡ VODAFONE ፡ ለሚ፟መ፟ራ፟ው ፡ SAFARICOM ፡ ለተባለው ፡ ቅንጅት ፡ ለ850 ፡ ሚልዮን ፡ ዶላር ፡ የቅድሚያ ፡ ክፍያ ፡ (እጅ ፡ መንሻ) ፡ ሲኰኳው ፥ ምዕራባውያን ፡ በወቅቱ ፡ ካሳዩት ፡ "ፀረ ፡ ኢትዮጵያ" ፡ አቋም ፡ ጋራ ፡ ፈጽሞ ፡ የማይጣጣም ፡ ድርጊት ፡ ከመኾኑም ፡ የባሰ፦ • ከምርጫው ፡ በፊት ፥ መንደር ፡ ገነን ፡ ዐቢይ ፡ አሕመድ፦ "መንግሥታውያን ፡ የንግድ ፡ ድርጅቶችን ፡ ዅሉ ፡ ወደ ፡ ግል ፡ ይዞታ ፡ እናዛውራለን" ፡ ሲሉ ፡ ያመለከቱት ፥ • ከምርጫ ፡ በዃላ ፡ ደግሞ ፥ እያደር ፡ የሚንሰራፋ ፡ የብዝበዛ ፡ ሥርዐት ፡ እንደ ፡ ተዘረጋ ፡ ይህ ፡ ድርጊት ፡ አስቀድሞ ፡ አረጋግጧል ። በዛሬው ፡ ዕለት ፥ መስከረም ፡ 26 ፡ ቀን ፡ 2014 ፡ ዓ.ም. ፥ የመቀመጫዎቹን ፡ 98% ፡ ፓርቲያቸው ፡ "ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.-ብልጽግና ፡ ፓርቲ-ሸኔ" ፡ በያዘበት ፥ ቀሪው ፡ 2% ፡ ደግሞ ፡ ከጥቂት ፡ ዓመት ፡ ወዲህ ፡ ሰፊ ፡ የመንግሥት ፡ ማወራኛ ፡ ዕድል ፡ የተሰጣቸው ፡ የ"አሯሯጭ" ፡ ፓርቲ ፡ ተወካዮችና ፡ አንዳንድ ፡ ተሰሚዎች ፡ ግለኞች ፡ በያዙት ፡ ባሻንጕሊቱ ፡ የተወካዮች ፡ ምክር ፡ ቤት ፥ መንደር ፡ ገነን ፡ ዐቢይ ፡ አሕመድ ፡ "የዐዲስ ፡ መንግሥት ፡ ምሥረታ" ፡ ንግግራቸውን ፡ አስሰምተዋል ። "Sovereign Fund" ፡ በሚል ፡ ሥያሜ ፡ በሚቋቋም ፡ ዐዲስ ፡ ተቋም ፡ አማካይነት ፥ ጠቅላላውን ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ እና ፡ መንግሥት ፡ ንብረት ፡ ባጪር ፡ ጊዜ ፡ ውስጥ ፡ በ200 ፡ ቢልዮን ፡ ዶላር ፡ ለውጭ ፡ ባለሀብቶች ፡ የመቸብቸብ ፡ ዕቀዳቸውን ፡ በቅርቡ ፡ ይፋ ፡ እንደሚያወጡ ፡ ገልጸዋል ። እንደተጠበቀው ፥ ትርፋማዎቹ ፡ የኢትዮጵያ ፡ አየር ፡ መንገድ ፣ ኢትዮቴሌኮም ፣ የኢትዮጵያ ፡ ኤሌትሪክ ፡ ኀይል ፡ ባለሥልጣን ፣ የውሃ ፡ ልማት ፡ ባለሥልጣን ፣ ሰፋፊ ፡ የዕርሻና ፡ የከተማ ፡ ቦታዎች ፣ የወርቅና ፡ የማዕድናት ፡ ቦታዎች ፣ የነዳጅና ፡ የኀይል ፡ ማመንጫዎች ፣ የሸንኰራ ፡ አገዳ ፡ ዕርሻዎችና ፡ የስኳር ፡ ማምረቻዎች ፣ ወዘተርፈ ፥ አሰፍስፈው ፡ ለሚጠብ፟ቁ፟ ፡ የውጭ ፡ መንግሥታትና ፡ የውጭ ፡ ባለሀብቶች ፡ በቅድሚያ ፡ ተመድበዋል ። ልዋጩን ፥ ለቅሬታ ፡ ይዘቱ ፡ መንደር ፡ ገነኖች ፡ ተፈላጊው ፡ ድጋፍና ፡ ጥበቃ ፡ ዅሉ ፡ በውጭ ፡ ኀይሎቹ ፡ እንደሚደረግላቸው ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ላይ ፡ በቅርቡ ፡ በደረሰው ፡ ግፍ ፡ ተረጋግጧል ። ይህ ፡ የሀገርና ፡ የሕዝብ ፡ ንብረት ፡ ብዝበዛ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ በሚፈጸምበት ፡ ዋዜማ ፥ በብሪታንያ ፡ ደግሞ ፥ የኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ የአንከርት ፡ ስልክ ፡ ("ሞባይል ፡ ፎን") ፡ አገልግሎት ፥ ሚያዝያ ፡ 27 ፡ ቀን ፡ 2013 ፡ ዓ.ም. ፡ በተከሠተ ፡ ሸር ፥ EE ፡ በተባለው ፡ ብሪታንያዊ ፡ የንግድ ፡ ድርጅት ፡ በግፍ ፡ ታግዶበታል ፡ (ዝርዝሩን ፡ እመርበቢያችን ፡ http://www.slttunhzb.net  ፡ ይመለከቷል) ። ለዚህ ፡ ግፍ ፡ ምክንያት ፡ የኾነው ፥ ሕጋዊ ፡ መንግሥት ፡ በኢትዮጵያ ፡ እስካልተቋቋመ ፡ ድረስ ፡ አንድም ፡ መንግሥታዊ ፡ ድርጅት ፡ ወደግል ፡ ይዞታ ፡ ሊዛወር ፡ አይገ፟ባ፟ም ፡ ሲል ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ደጋግሞ ፡ ያስሰማው ፡ ርትዓዊ ፡ አቋሙ ፡ መኾኑ ፡ ግልጽ ፡ ነው ። ይህ ፡ የብቀላ ፡ ግፍ ፡ የተባበሩት ፡ መንግሥታት ፡ ድርጅትን ፡ የሰብኣዊ ፡ መብት ፡ ብሔራዊ ፡ ድንጋጌ ፥ አንቀጽ ፡ 19 ፥ በገቢር ፡ ረምርሟል ። የሠኔ ፡ 14 ፡ ቀን ፡ 2013 ፡ ዓ.ም. ፡ ግብዝ ፡ ምርጫ ፥ የቀደመውን ፡ ፀረ ፡ ሀገር ፡ ግብር ፡ በተጠናከረና ፡ በከፋ፟ ፡ መንገድ ፡ ለመቀጠል ፡ ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቀሬታ ፡ ይዘት ፡ ዐዲስ ፡ የጥፋት ፡ ምዕራፍ ፡ የሚከፍትለትን ፡ ያኽል ፥ የሕዝብን ፡ ተቃውሞ ፡ በማባባስ ፥ ቅራኔውን ፡ አጕልቶ ፥ ላጠቃላይ ፡ ፍርሰቱም ፡ ይዳርገዋል ። እስካኹን ፥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቀሬታ ፡ ይዘት ፥ ግንዱ ፡ እንደተጠረበ ፡ ዛፍ ፥ ለመደ፟ርመስ ፥ በትንሹ ፡ የሚገፋውን ፡ ኀይል ፡ ይጠ፟ባበ፟ቅ ፡ የነበረው ፤ ዛሬ ፥ ይህን ፡ ኀይል ፡ በግብዝ ፡ ምርጫው ፡ ማግስት ፡ በቂ ፡ አካል ፡ ሰጥቶት ፡ ይገኛል ። ክፉ ፡ ሥራ ፡ ዅሉ ፥ ጠሩን ፡ በውስጡ ፡ የያዘ ፡ በመኾኑ ፥ ጥንታዊት ፡ ኢትዮጵያን ፡ እናፈርስበታለን ፡ ብለው ፡ ያበጁት ፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ይዘት ፥ እንሆ ፡ ቀድሞ ፡ ተፍረክርኳል ። ዋናው ፡ እጀታው ፡ ፋሺስቱ ፡ ወያኔ-ሕ.ወ.ሐ.ት. ፡ ላልቶ ፡ ሲወልቅ ፥ "ብቻዬን ፡ አልወልቅም" ፡ በሚል ፡ ከተስፋቢስነት ፡ በመነጨ ፡ ምቀኝነት ፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቅሬታ ፡ ይዘትን ፡ ቀጥቅጦ ፡ ለማስጣል ፡ በሰይጣናዊ ፡ እልክና ፡ ጽናት ፡ ጦርነት ፡ አንሥቶበታል ፥ ንጹሓንንም ፡ በገፍ ፡ ፈጅቷል ፣ አፈናቅሏልም ። "ባንድ ፡ ድንጋይ ፡ ኹለት ፡ ወፎችን ፡ መግደል" ፡ በሚል ፡ ስልት ፥ የምልክዮሽ ፡ ኀይሎችም ፥ እነዚህን ፡ ኹለት ፡ የጥፋት ፡ ኀይሎች ፡ በጣልቃ ፡ ገብነት ፡ ለማሸማገልና ፡ በኢትዮጵያ ፡ ዕጣ ፡ ፈንታ ፡ ላይ ፡ ለመወሰን ፡ ጣልቃ ፡ መግቢያ ፡ ፍንጭ ፡ ስላገኙ ፥ እፊት ፡ እፊት ፡ ማለትን ፡ ይዘዋል ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ እና ፡ ሰራዊቱ ፡ ይህን ፡ የምልከኞችን ፡ (የ"ኢምፔሪያሊስቶችን") ፡ ክፉ ፡ ደባ ፡ ቀድመው ፡ ማክሸፍ ፡ ይኖርባቸዋል ። ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቅሬታ ፡ ይዘት ፡ የሚታዘንለት ፡ አይደለም ፤ ምክንያቱም፦ • በኅዳር ፡ ወር ፡ 2013 ፡ ዓ.ም. ፡ በኢትዮጵያ ፡ ሀገራዊ ፡ ሰራዊት ፡ ድል ፡ የኾነውን ፡ የወያኔ-ሕ.ወ.ሐ.ት. ፡ ፋሺስታዊ ፡ ኀይል ፥ ስምንት ፡ ወራት ፡ ባልሞላ ፡ ጊዜ ፡ ውስጥ ፡ ዳግም ፡ እንዲያንሰራራ ፥ • የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ እማያባራ ፡ የሥልጣን ፡ ጦርነት ፡ ውስጥ ፡ እንዲማገድና ፡ ጥፋቱ ፡ እንዲረጋገጥ ፥ ከከባድ ፡ የጦር ፡ መሣሪያ ፡ ጋራ ፥ ከ200 ፡ ቢልዮን ፡ ብር ፡ ያላነሰ ፡ የሀገር ፡ ሀብትን ፡ ለወያኔ-ሕ.ወ.ሐ.ት. ፡ ያፈሰሰለት ፡ ቅሬታ ፡ ይዘቱን ፡ የሚመራው ፡ የ"ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.-ብልጽግና ፡ ፓርቲ-ሸኔ" ፡ መንደር ፡ ገነን ፡ አገዛዝ ፡ ራሱ ፡ ነው ፤ ይህኑም ፡ በአለቃው ፡ በዶክተር ፡ ዐቢይ ፡ አሕመድ ፡ አንደበት ፡ አምኗል ። ማመኑ ፡ ግን ፥ የጸጸትና ፡ የንስሓ ፡ ሳይኾን ፥ የቅሬታ ፡ ይዘቱን ፡ ዕድሜ ፡ ማራዘሚያና ፡ ቀሪ ፡ ሥራውን ፡ ማስለጫ ፡ ስልቱ ፡ መሥራቱን ፡ ማረጋገጡ ፡ ይመስላል ። ዛሬ ፡ ባደረገውም ፡ ሹም ፡ ሽር ፥ የወያኔ-ሕ.ወ.ሐ.ት. ፡ አባልና ፥ እንደ ፡ ዶክተር/ኮሎኔል ፡ ዐቢይ ፡ አሕመድ ፡ ዅሉ ፥ የወያኔ-ሕ.ወ.ሐ.ት. ፡ አገዛዝ ፡ ቀንደኛ ፡ የሰላይ ፡ አለቃ ፡ የነበረውን ፥ በቅርቡ ፡ ደግሞ ፡ የ"ትግራይ ፡ ክልል" ፡ ጊዜያዊ ፡ አስተዳደር ፡ ሊቀ ፡ መንበር ፡ ኾኖ ፥ እላይ ፡ የተገለጹትን ፡ ልዩ ፡ ልዩ ፡ ድጋፎች ፡ ለወያኔ-ሕ.ወ.ሐ.ት. ፡ ያሸጋገረውን ፡ ዶክተር/ኮሎኔል ፡ አብርሃም ፡ በላይ ፡ የቅሬታ ፡ ይዘቱ ፡ "የመከላከያ ፡ ሚኒስትር" ፡ ብሎ ፡ ሠይሞታል ። በሀገሪቱ ፡ ላይ ፡ የባሰ ፡ ጥፋት ፡ ከመድረሱ ፡ በፊት ፥ የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፥ ለጠፋው ፡ ሕይወትና ፡ የሀገር ፡ ሀብት ፥ የቅሬታ ፡ ይዘቱን ፡ ኀላፊዎች ፡ ተጠያቂዎች ፡ አድርጎ ፡ በሀገር ፡ ክዳት ፡ ወንጀል ፡ ለፍርድ ፡ ሊያቀርባቸው ፡ ይገ፟ባ፟ል ፡ ሲል ፡ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ ጥሪውን ፡ ያስተላልፋል ። ኢ.ሀ.ሥ.አ. ፡ በበኩሉ ፥ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፡ ቅሬታ ፡ ይዘት ፡ ላዲስ ፡ ሕገ ፡ መንግሥት ፡ ረቀቃና ፡ ጸደቃ ፡ ለሚውል ፡ የመሸጋገሪያ ፡ መንግሥት ፡ ሰላማዊ ፡ ምሥረታ ፡ ቀና፟ ፡ አስተያየት ፡ ይኖረው ፡ ይኾናል ፡ በሚል ፡ ተስፋ ፡ ላለፉት ፡ ሦስት ፡ ዓመታት ፡ ላቀረበለት ፡ ጥያቄዎች ፡ ዅሉ ፥ መልሱን ፥ ከጉሊሶ ፡ እስከ ፡ ወሊሶ ፣ ከማንዱራ ፡ እስከ ፡ ጉራ፟ ፡ ፈርዳ ፣ ከአጣዬ ፡ እስከ ፡ ከሚሴ ፣ ከሆሮ፟ ፡ ጕድሩ ፡ እስከ ፡ ሊሙ ፥ አኹን ፡ ደግሞ ፡ ከደባርቅ ፡ እስከ ፡ ሐይቅ ፣ ከመቀሌ ፡ እስከ ፡ በራሕሌ ፣ ከሰቈጣ ፡ እስከ ፡ ጭና ፥ ከነፋስ ፡ መውጫ ፡ እስከ ፡ ቆቦ፟ ፡ የንጹሓንን ፡ ደም ፡ እንደ ፡ ጐርፍ ፡ በማፍሰስ ፡ አሉታውን ፡ ደጋግሞ ፡ ስላደረሰው ፥ ቅሬታ ፡ ይዘቱን ፡ በተመለከተ ፥ እንደ ፡ ወያኔ-ሕ.ወ.ሐ.ት. ፡ ዅሉ ፡ ከመወ፟ገድ ፡ በቀር ፡ ከእንግዲህ ፡ ሌላ ፡ ማማረጫ ፡ እንደሌለ ፡ ደምድሟል ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብም ፡ ዐዲስ ፡ ሕገ ፡ መንግሥቱን ፡ ከመሥራት ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ ማማረጫ ፡ የለው ፤ ለዚህም ፡ በመላ፟ ፡ ሀገሩ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ላይ ፡ እግዚእናውን ፡ በገቢር ፡ ማረጋገጥ ፥ "ፓርቲዎች"ን ፡ ደግሞ ፡ የእግዚኡ ፡ ሕዝብ ፡ አሽከርነታቸውን ፡ በማወቅ ፡ ከምልክዮሽ ፡ አሻንጕሊትነታቸው ፡ እንዲወጡ ፡ ሊነግራቸው ፡ ይገ፟ባ፟ል ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ እግዚእናውን ፡ ለማስከበርና ፡ ዐዲስ ፡ ሕገ ፡ መንግሥቱን ፡ ለመሥራት ፡ የተያያዘውን ፡ ትግል ፡ በማጠናከር ፥ ባጪር ፡ ጊዜ ፡ ውስጥ ፡ በድል ፡ ለመወጣት ፡ ከመቼውም ፡ የበለጠ ፡ ኹኔታው ፡ ዛሬ ፡ ተመቻችቶለታል ። የኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፥ የጸጥታና ፡ የጦር ፡ ሰራዊቶቹን ፡ እትእዛዙ ፡ ሥር ፡ በማስገባት ፥ በቅጽበታዊ ፡ ፍጥነት ፡ ወደ ፡ ቈራጥ ፡ የመፍትሔ ፡ ክንዋኔ ፡ በአንድነት ፡ ማምራት ፡ ይኖርበታል ፨ የጊዜያዊ ፡ ፈጻሚ ፡ ምክር ፡ ጽሕፈት ፡ ቤት ፥ ኢ.ሀ.ሥ.አ. ። ------- [የኅዳግ  ፡ ምልክቶች] ⁽1⁾ የኢትዮጵያ ፡ ፌዴራላዊ ፡ ዴሞክራሲያዊ ፡ ሪፓብሊክ ፡ (ኢ.ፌ.ዴ.ሪ.) ። ⁽2⁾ ይዘት  ፤ በግእዝ  ፡ 'እኅዘት'  ፥ አለሥልጣኑ  ፥ መንግሥታዊ  ፡ ኀይልን  ፡ በእጀ  ፡ መናኛ  ፡ የጨበጠ  ፡ ዐምባ  ፡ ገነን  ፡ አገዛዝ  ፡ ("régime")  ። ⁽3⁾ ሕዝባዊ ፡ ወያኔ ፡ ሐርነት ፡ ትግራይ ፡ (ሕ.ወ.ሐ.ት.) ። ⁽4⁾ ዐማራ ፡ (ዐም ፡ ሐራ) ፤ ነጻ ፡ ሕዝብ ፥ ኢትዮጵያን ፡ የሠራ ፡ የመላ፟ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ሕዝብ ፡ የሀገራዊነት ፡ ወይም ፡ የሀገር ፡ ባለቤትነት ፡ ስም ፡ (citizenry) ። ===================================================== የኢትዮጵያውያን  ፡ ሀገራዊ  ፡ ሥልጡንሕዝባዊ  ፡ አንድነት  ። ETHIOPIANS' CITIZEN DEMOCRATIC UNION www.slttunhzb.net sh1@ttomar.net _______ ዜመ_ኢ-1_20140126_እንግሊዝኛ PRESS RELEASE (English translation of the Amharic original) Salvaging a Moribund Régime? The F.D.R.E. ⁽5⁾ remnant régime that is founded on a foreign imposed unlawful "constitution" cannot legitimise its power through fake elections. _______ London, 06th October 2021. The Ethiopians' Citizen Democratic Union (E.C.D.U.) declares to the Ethiopian People and the States and governments of the World that the fake elections that took place in Ethiopia on the 21st of June 2021 were called by an unlawful régime, founded on a nihilistic and foreign imposed "constitution" that: • does not recognise the unity and sovereignty of the Ethiopian People; • has implemented an Apartheid system on the country; • attempts to make Ethiopia an ownerless country; consequently, the results of the elections are null and void. They will not provide the F.D.R.E. remnant régime with the legitimacy of authority it is craving for, nor will it reverse the process of deliquescence the régime is already engaged in. As the "new government" that is announced to be formed on the 6th of October 2021 is drawn from the same remnant régime – minus its decapitated head the T.P.L.F. ⁽6⁾ – that is suffering from the cancer of corruption, soaking in the blood of innocents for over thirty years; it has no hope of remission. In an indignant stratagem wholly designed to salvage a moribund régime, and having the benediction and active participation of some Western powers, the F.D.R.E. remnant régime is engaged, for the past many months, in an exercise of deception aimed at the population, whereby the fascist T.P.L.F. is presented as the "emissary of Western Imperialism" in Ethiopia, while the F.D.R.E. remnant régime is presented as the sole "defender" of Ethiopia. Starting a few months before the elections in question, the godfather of the F.D.R.E. régime the United States of America and a few other Western Countries, have used different pretexts to issue a series of "anti-Ethiopian" official declarations widely relayed and well publicised by their media, in a ruse designed to galvanise the Ethiopian public into rallying around the fledgeling F.D.R.E. remnant régime. One such particularly high profile instance was the "irresponsible" public encouragement given on live television, in the presence of the World's media, by the then US president Trump to the Republic of Egypt to bomb the dam Ethiopia is completing on the Blue Nile. Another proxy-mediated lethal act was the invasion of Ethiopian territory by the armed forces of the beleaguered Sudanese Transitional Government in which many civilians and military have been killed, and numerous property damaged or plundered. This set of indignant acts aiming to salvage a moribund régime has devalued by the same token the standing of these Western nations' respective foreign policies before the eyes of the international community. Their attempts will fail to achieve anything with respect to the legitimation of the F.D.R.E. remnant régime's power. Worse still, the direct or indirect implication of these foreign forces in the unnecessary loss of human lives in Ethiopia is now verified. The E.C.D.U. strongly condemns these unlawful acts of interference in the internal affairs of Ethiopia. For the past three years, the "E.P.R.D.F.-Prosperity Party-Shené" led dictatorial rule has been: • dislocating the whole country, • killing and displacing millions of innocent civilians while implementing its anti-citizen/anti-Amhara ⁽7⁾ policy, • killing or imprisoning those that oppose it, • carrying out the despoliation of the country's wealth and the people's patrimony, and committing other crimes openly, without any attempt to conceal them. In May 2021, the dictatorial régime has given away a significant share of the Ethiopian mobile phone market to the SAFARICOM consortium led by the British company VODAFONE for an advance payment (present) of 850 million dollar, in complete contradiction with the "anti-Ethiopian" declamations that were coming from the West at the time. Furthermore: • the announcement by dictator ዐቢይ ፡ አሕመድ / Abiy Ahmed, prior to the elections, of his intention to privatise all existing public enterprises, • the intensification of the scramble for public assets, after the election, were all predicated by that initial give away. Today 06th October 2021, dictator Abiy Ahmed has made his inaugural speech before the puppet house of representatives where 98% of the seats are held by his "Prosperity Party", and the remaining 2% by representatives of "pacemaker" parties or individual opinion makers that had all been given privileged State media coverage over the past few years. In his speech, he has announced of his intention to launch a so-called "Sovereign Fund", the purpose of which will be to sell, in a short period of time, all State assets to foreign buyers for an estimated 200 Billion dollars. As expected, profitable public enterprises that include Ethiopian Airlines, EthioTelecom, Ethiopian Electric Light and Power Authority, Ethiopian Water Authority, large tracts of agricultural as well as urban land, gold mines and other precious metal mines, oil deposits and energy sources, sugar cane plantations and sugar factories, etc., are all pre-allocated to those foreign powers and foreign investors that have been coveting them. In exchange, the rulers of the remnant regime are guaranteed the support and protection of these external forces as the recent injustice committed against the E.C.D.U. has plainly confirmed. Indeed, in a machination that came to fruition on the 05th of May 2021, the mobile phone service of the E.C.D.U. has been suspended by the British company EE (please refer to our website: http://www.slttunhzb.net ), on the eve of the above give away of public assets in Ethiopia. It is clear that the reason for this attack is the repeatedly stated and rightful position of the E.C.D.U. that no privatisation of public enterprise in Ethiopia should take place in the absence of a legitimate government. This retaliatory action against the E.C.D.U. is in complete breach of Article 19 of the United Nations' Universal Declaration of Human Rights. The 21st of June 2021 fake elections, while ushering in a new chapter for the F.D.R.E. remnant régime to commit further crimes, it will also drive it to its complete downfall by exacerbating the People's opposition. Until now, the F.D.R.E. remnant régime was similar to a tree with its base chipped away and awaiting the force that is going to shove it and bring it down; on the wake of the fake elections, the remnant régime has given enough body to such a force. Evil intentioned deeds always hold inherently their own nemesis; the F.D.R.E. régime was established to bring about the downfall of ancient Ethiopia, and behold, the instrument of that downfall crumbled first. Its main handle, the fascist Weyané-T.P.L.F. having been dislocated, it is now jealously and hopelessly waging a war against the remnant régime with a devilish determination to dismantle it. In so doing it has killed and displaced numerous innocent civilians. To kill two birds with one stone, imperialist forces are using this opportunity to further interfere by offering to arbitrate between these two destructive forces in a bid to decide on the destiny of Ethiopia. The Ethiopian People and armed forces must take the initiative to rapidly thwart this evil scheme of imperialists. There are no reasons to lament over the predicament of the "E.P.R.D.F.-Prosperity Party-Shené" led dictatorial remnant régime since: • it has rehabilitated the fascist Weyané-T.P.L.F. forces, less than eight months after they had been annihilated by the Ethiopian armed forces, • it has plunged the Ethiopian People in an endless civil war that will bring about their destruction, by syphoning to the Weyané-T.P.L.F. over 200 million Br (around 4 billion dollars) worth of support, together with heavy weaponry, as acknowledged by its leader Dr. Abiy Ahmed. The admission is not out of guilt but most probably to confirm the success of his tactics to extend the lifespan of the remnant régime and complete the unfinished business. In the cabinet reshuffle carried out today, a member of Weyané-T.P.L.F. and, as Dr / Colonel Abiy Ahmed himself, a former chief of intelligence of the Weyané-T.P.L.F. dictatorship, and as the recent "President" of the "transitional administration of the Tgray Homeland" the person who supervised the above mentioned transfer of funds and heavy armament to the Weyané-T.P.L.F., Dr / Colonel አብርሃም ፡ በላይ / Abrham Belay has become the remnant régime's new Defence Minister. That is why the E.C.D.U. calls once again upon the Ethiopian People to apprehend the leadership of the remnant régime in order to present them before the law courts for high treason, before irreparable damage is done to the country. On its part, the E.C.D.U. had hoped that the F.D.R.E. remnant régime would respond with a certain goodwill to the repeated calls for the peaceful establishment of a transitional government leading to the drafting and adoption of a new Constitution for the country; instead, the remnant régime has expressed its refusal with torrents of blood shed from ጉሊሶ / Gouliso to ወሊሶ / Weliso, from ማንዱራ /Mandoura to ጉራ፟ ፡ ፈርዳ / Gourra Ferda, from አጣዬ / At፟ayé to ከሚሴ / Kemisé, from ሆሮ፟ ፡ ጕድሩ / Horro Gwdrou to ሊሙ / Limou, and more recently, from ደባርቅ / Debarq to ሐይቅ / Hayq, from መቀሌ / Meqelé to በራሕሌ / Berah፟lé, from ሰቈጣ / Seqwet፟a to ጭና / Ttchna, from ነፋስ ፡ መውጫ / Nefas Mewttcha to ቆቦ፟ / Qobbo. The E.C.D.U. has now come to the conclusion that there is no alternative but to remove the F.D.R.E. remnant régime, together with the Weyané-T.P.L.F.. The Ethiopian People too have no alternative but to adopt a new Constitution; to that effect, they must concretely reaffirm their sovereignty over the whole territory of Ethiopia, and remind political parties that their rightful role is that of servants of the sovereign People and not that of puppets of imperialism. The present situation is more than ever ideal for the People to achieve their goals of reaffirming their sovereignty and establishing a new Constitution, in a short period of time, by intensifying the struggle. The Ethiopian People must prepare themselves for rapid and decisive steps to be taken in unison towards the resolution of the current political crisis, by bringing under their command the security forces and the armed forces ፨ Secretariat of the Provisional Executive Council, E.C.D.U. ------- [FOOTNOTES] ⁽5⁾ F.D.R.E.: Federal Democratic Republic of Ethiopia. ⁽6⁾ T.P.L.F. : Tgray People's Liberation Front. ⁽7⁾ Amhara / ዐምሐራ : the name of the whole Ethiopian citizenry that made Ethiopia. Contrary to what the "mean"-stream media knowingly and falsely propagate ad nauseam : it is not the name of an ethnic group. ====================================================== የኢትዮጵያውያን  ፡ ሀገራዊ  ፡ ሥልጡንሕዝባዊ  ፡ አንድነት  ። UNION CITOYENNE DÉMOCRATIQUE DES ÉTHIOPIENS www.slttunhzb.net sh1@ttomar.net _______ ዜመ_ኢ-1_20140126_ፈረንሳይኛ COMMUNIQUÉ DE PRESSE (traduction française de l'original en amharique) Sauvetage d'un régime moribond ? Le régime résiduaire R.F.D.E. ⁽8⁾, qui est établi par une "constitution" illégitime imposée par l'étranger, ne peut légitimer son pouvoir par un simulacre d'élections. _______ Londres, le 6 octobre 2021. L'Union Citoyenne Démocratique des Éthiopiens (U.C.D.E.) déclare au Peuple Éthiopien et aux États et gouvernements du Monde entier, que le simulacre d'élections qui a eu lieu en Éthiopie le 21 juin 2021 a été organisé par un régime illégitime, établi par une "constitution" nihiliste et imposée par l'étranger, qui : • ne reconnaît pas l'unité et la souveraineté du Peuple Éthiopien, • a implanté un système d'Apartheid dans le pays, • tente de faire de l'Éthiopie un pays sans titulaire ; les résultats des élections sont par conséquent nuls et non-avenus. Ils ne donneront pas au régime résiduaire R.F.D.E. la légitimité d'autorité qu'il souhaite, ni renverser le processus de déliquescence dans lequel il est déjà bien engagé. Comme le "nouveau gouvernement" annoncé pour le 06 octobre 2021 émane du même régime résiduaire – soustraction faite de son chef décapité le F.P.L.T. ⁽9⁾ – atteint du cancer de la corruption, et trempé depuis plus de trente années dans le sang d'innocents ; il n'a aucun espoir de rémission. Suivant un stratagème indigne qui bénéficie de la bénédiction et de la participation active de certaines puissances occidentales, visant à le sauvegarder, le régime résiduaire R.F.D.E. moribond est engagé dans un exercice de déception destiné à la population, en faisant passer le F.P.L.T. pour "l'émissaire de l'impérialisme occidental" en Éthiopie, alors que le régime résiduaire R.F.D.E. est présenté comme l'unique "défenseur" de l'Éthiopie. Quelques mois avant les élections en question, le parrain du régime, les États Unis d'Amérique, et certaines puissances occidentales ont choisi différents prétextes pour faire des déclarations d'apparence particulièrement "anti-éthiopiennes" et très largement diffusées par leurs media, dont le but a été de galvaniser le public Éthiopien afin qu'il se rallie autour du régime résiduaire R.F.D.E. chancelant. Pour ne citer que quelques instances notoires, la déclaration irresponsable faite par le président américain de l'époque, M. Donald Trump, en directe à la télévision et en présence des média du monde entier, encourageant le président de la République d'Égypte, le général Elsisi, à aller bombarder le barrage hydro-électrique que l'Éthiopie voisine construit sur le Nil Bleu, en est une parfaite illustration. La récente invasion et occupation de territoire frontalier éthiopien par les armées du fragile gouvernement transitoire soudanais lesquelles ont aussi tué des civils et des militaires, ainsi que saccagé et pillé des propriétés, en est une autre illustration d'une agression par procuration, cette fois meurtrière. L'ensemble de ces actes indignes venant de la part de ces puissances occidentales a dévalorisé le prestige de leurs politiques étrangères aux yeux de l'opinion publique internationale. En outre, leur tentative n'aura pas le succès escompté en ce qui concerne la légitimation du régime résiduaire R.F.D.E.. Pire encore, l'implication directe ou indirecte de ces forces étrangères dans la perte inutile de vies humaines en Éthiopie est maintenant vérifiée. L'U.C.D.E. condamne fermement ces actes illégaux d'interférence dans les affaires intérieures de l'Éthiopie. Durant les trois dernières années, la dictature du parti "F.P.R.D.E – Prosperity Party – Shené" a : • disloqué le pays entier, • tué et déplacé des millions de civils innocents au nom de sa politique anti-citoyenne / anti-Amhara ⁽10⁾, • tué ou emprisonné ceux qui se sont opposés à lui, • entamé la spoliation des richesses du pays et du patrimoine du Peuple, et commis ouvertement d'autres crimes encore, sans aucune tentative de les dissimuler. Au mois de mai 2021, le régime dictatorial a livré une part significative du marché éthiopien du téléphone mobile au consortium SAFARICOM qui est dirigé par le britannique VODAFONE, moyennant le paiement d'une avance (cadeau) de 850 millions de dollars, en contradiction totale avec les déclamations "anti-éthiopiennes" venant au même moment de l'Occident. De plus : • l'annonce faite par le dictateur ዐቢይ ፡ አሕመድ / Abiy Ahmed de son intention de privatiser toutes les entreprises publiques éthiopiennes, • l'intensification de la ruée vers les avoirs publics au lendemain des élections, étaient toutes annoncées par ce transfert initial. Le dictateur Abiy Ahmed a, aujourd'hui 06 octobre 2021, prononcé son discours inaugural devant la chambre des représentants fantoche où 98% des sièges sont occupés par son "F.P.R.D.E – Prosperity Party – Shené", les restants 2% par les représentants de partis "meneurs de train" et quelques individus influents qui ont bénéficié depuis quelques années d'une couverture médiatique publique privilégiée. Dans son discours, il a annoncé son intention de lancer prochainement ce qu'il a appelé un "Sovereign Fund" ou "Fonds Souverain" dont l'objectif est de vendre tous les avoirs de l'État à des acheteurs étrangers pour un montant qu'il a estimé à plus de 200 milliards de dollars. Comme prévu, des entreprises publiques profitables telles Ethiopian Airlines, EthioTelecom, l'Autorité de l'Électricité Éthiopienne, l'Autorité des Eaux Éthiopienne, de vastes terres agricoles et urbaines, des mines d'or et autres métaux précieux, des réserves d'hydrocarbures et de ressources énergétiques, des plantations de cannes à sucre ainsi que des sucreries, etc., sont tous pré-alloués à des puissances étrangères et des investisseurs étrangers qui les ont longtemps convoités. En échange, les dirigeants du régime résiduaire ont l'assurance du soutien et de la protection sans faille de ces derniers, comme la récente injustice commise à l'encontre de U.C.D.E. l'a si visiblement illustrée. En effet, dans une machination qui a porté son fruit le 05 mai 2021, le service de téléphone mobile de l'U.C.D.E. a été suspendu par la société britannique EE (pour plus de détail, veuillez s'il vous plaît vous référer à notre site : http://www.slttunhzb.net ) quelques jours avant le transfert des fonds publics en Éthiopie. Il est clair que la raison de cette attaque est la position justifiée et plusieurs fois réitérée de l'U.C.D.E. selon laquelle aucune privatisation d'entreprises publiques ne devrait avoir lieu en l'absence d'un gouvernement légitime. Cette mesure de rétorsion visant l'U.C.D.E. constitue une violation de l'article 19 de la déclaration universelle des droits humains de l'Organisation des Nations Unies. Le simulacre d'élections du 21 juin 2021, en même temps qu'il a ouvert au régime résiduaire R.F.D.E. un nouveau chapitre pour commettre de nouveaux crimes, il finira aussi par mener le régime vers sa perte en exacerbant l'opposition du Peuple. Jusqu'à présent, le régime résiduaire R.F.D.E. était semblable à un arbre dont le tronc est taillé à sa base, à la merci d'une simple poussée qui peut provoquer sa chute ; au lendemain du simulacre d'élections, le régime résiduaire a donné assez de corps à cette force. Toute action malfaisante détient en elle-même son Némésis ; le régime résiduaire R.F.D.E. était établi avec l'objectif de provoquer la chute de l'Éthiopie millénaire ; or, voici que l'instrument par lequel cette chute devait survenir s'est écroulé le premier. Sa principale manche, le fasciste Weyané-F.P.L.T. s'étant disloqué, il mène maintenant sa guerre contre le régime résiduaire R.F.D.E. avec une farouche détermination motivée par un fort sentiment de jalousie et de désespoir. Ce faisant, il a causé la mort et le déplacement de nombreux civils innocents. D'une pierre deux coups, les forces impérialistes veulent désormais en profiter pour jouer les arbitres entre ces deux forces destructrices, dans le but de décider sur le sort de l'Éthiopie. Le Peuple Éthiopien et ses forces armées doivent prendre l'initiative pour rapidement contrecarrer ce vicieux projet des impérialistes. Il n'y a aucune raison pour se plaindre sur le sort du régime résiduaire R.F.D.E. dirigé par le "F.P.R.D.E – Prosperity Party – Shené", car : • c'est lui qui a réhabilité les forces du fasciste Weyané-F.P.L.T., huit mois après qu'elles ont été totalement annihilées par les forces armées éthiopiennes, • c'est aussi lui qui a plongé le Peuple Éthiopien dans une guerre civile larvée pour le mener à sa destruction, en livrant au Weyané-F.P.L.T. plus de 200 milliards de Br (l'équivalent de 3.5 milliards d'euros) sous forme de soutien, ainsi que de l'armement lourd, comme l'a reconnu son dirigeant, le D. Abiy Ahmed. Cette admission n'est pas l'expression d'un quelconque remords, mais plutôt celle d'une satisfaction de voir réussir la tactique visant à rallonger encore la durée de vie du régime résiduaire afin de "régler les affaires" restantes. Dans un remaniement du cabinet ministériel effectué aujourd'hui, un membre du Weyané-F.P.L.T. et, comme le docteur/colonel Abiy Ahmed, lui aussi ancien chef de l'intelligence de la dictature Weyané-F.P.L.T., puis dernièrement "Président" de "l'administration transitoire du Tgray Homeland" qui a supervisé les transferts de fonds et armements lourds mentionnés ci-dessus, le docteur/colonel አብርሃም ፡ በላይ / Abrham Belay est devenu le nouveau ministre de la défense du régime résiduaire. C'est pourquoi l'U.C.D.E. renouvelle son appel au Peuple Éthiopien à mettre la main sur la direction du régime résiduaire, afin de la présenter devant la justice pour haute trahison, avant que des dommages irréparables ne soient faits au pays. Pour sa part, l'U.C.D.E. avait espéré l'expression d'une certaine bonne volonté de la part du régime résiduaire R.F.D.E. aux appels répétés concernant l'établissement pacifique d'un gouvernement de transition conduisant à l'élaboration et adoption d'une nouvelle Constitution pour le pays ; à la place, le régime résiduaire lui a signifié son refus par des torrents de sang déversés de ጉሊሶ / Gouliso à ወሊሶ / Weliso, de ማንዱራ / Mandoura à ጉራ፟ ፡ ፈርዳ / Gourra Ferda, de አጣዬ / At፟ayé à ከሚሴ / Kemisé, de ሆሮ፟ ፡ ጕድሩ / Horro Gwdrou à ሊሙ / Limou, et plus récemment, de ደባርቅ / Debarq à ሐይቅ / Hayq, de መቀሌ / Meqelé à በራሕሌ / Berah፟lé, de ሰቈጣ / Seqwet፟a à ጭና / Ttchna, de ነፋስ ፡ መውጫ / Nefas Mewttcha à ቆቦ፟ / Qobbo. L'U.C.D.E. en est maintenant arrivé à conclure qu'il n'y a plus d'autre alternative que d'abolir le régime résiduaire R.F.D.E. au même titre que le Weyané-F.P.L.T.. Le Peuple Éthiopien aussi n'a pas d'autre alternative que d'adopter une nouvelle Constitution ; à cet effet, il doit concrètement réaffirmer sa souveraineté sur la totalité du territoire éthiopien, et rappeler aux partis politiques que leur vrai rôle est celui de serviteurs du Peuple souverain et non celui de marionnettes de l'impérialisme. La situation présente est plus que jamais propice pour le Peuple Éthiopien à réaliser enfin ses objectifs de réaffirmation de sa souveraineté et à adopter une nouvelle constitution dans un court laps de temps, en intensifiant sa lutte. Pour cela, le Peuple Éthiopien doit rapidement être prêt à prendre à l'unisson les pas décisifs vers la résolution des problèmes politiques du pays, en amenant sous son contrôle les forces de sécurité et les forces armées ፨ Secrétariat du Conseil Exécutif Provisoire, U.C.D.E. _______ [NOTES DE BAS DE PAGES] ⁽8⁾ R.F.D.E.: République Fédérale Démocratique d’Éthiopie. ⁽9⁾ F.P.L.T. : Front Populaire de Libération du Tgray. ⁽10⁾ Amhara / ዐምሐራ : nom de l'ensemble du peuple citoyen qui a constitué l'Éthiopie. Contrairement à ce que les média "mean"-stream propagent intentionnellement et faussement ad nauseam : il ne s'agit pas du nom d'un groupe ethnique.