Awdeqelem text processor•traitement de text Awdeqelem DOWNLOAD

• ዐውደ፡ቀለም፥ ነጻው፡ኢትዮጵያዊ፡የጽሑፍ፡ማምረቻ፡(ለዊንዶውዝ)፤
  ዐዲሱን፡ክለሳ፡1.3፡ይቅዱ።
• The latest version (v.1.3) of AwdeQelem, the free Ethiopian text processor (for Windows)
.
• La dernière version (v.1.3) de Awdeqelem, le traitement de texte éthiopien gratuit (pour Windows).

 ‣ የዐውደ፡ቀለም፡መመሪያ
  AwdeQelem user's manual | manuel d'utilisation de AwdeQelem (PDF)

የ"ዐውደ፡ቀለም"፡መርበቢያ፡awdeqelem.net፡
ከነሐሴ፡2011፡ዓ.ም.፡አንሥቶ፡አላግባብ፡ቢታገድም፥ ባለቤቱ፡አቶ፡ወሌ፡ነጋ፡እንዳስታወቁን፥ ከሚያዝያ፡2013፡ዓ.ም.፡አንሥቶ፥ በዐዲሱ፡አድራሻው፡በ፦

    http://www.awde-qelem.net

ሥራውን፡እንደሚቀጥል፡ገልጸዋል።
የመግለጫቸው፡ሙሉ፡ቃል፡እንደሚከተለው፡ነው፦


«የዐውደ ፡ ቀለም ፡ መርበቢያ፥ http://www.awdeqelem.net ፡ ኹለት ፡ የመርበቢያ ፡ አከራዮች ፡ magic.fr ፡ እና ፡ hostinger.com ፡ የተባሉ ፡ ድርጅቶች ፡ በግብር ፡ ዐበርነት ፡ በፈጸሙት ፡ ተንኰል ፡ ተጠልፎ ፡ ለኹለተኛ ፡ ዓመት ፡ ካገልግሎት ፡ ውጭ ፡ ኾኗል። ችግሩን ፡ ICANN ፡ ለተባለው ፡ አህጉራዊ ፡ የInternet ፡ ባለሥልጣን ፡ ተቋም ፡ ብናቀርበውም፥ ይህኛው፦ "ምንም ፡ ማድረግ ፡ አልችልም" ፡ የሚል ፡ አድሏዊ ፡ መልስን ፡ በመስጠቱ፥ ግልጽ ፡ የኾነ ፡ የስርጀታ ፡ ግብሩ ፡ እስኪከሽፍ ፡ ድረስ፥ ዐዲሱ ፡ መርበቢያችንን ፡ እ፦

    http://www.awde-qelem.net

ከፍተናል። ላልሰሙ ፡ እንድታሰሙልን ፡ በትሕትና ፡ እንለምናለን።»



"ዐውደ፡ቀለም"፡የተባለውን፡መግበር፡ኢ.ሀ.ሥ.አ.፡ስለሚሠራበትና፡ያገልግሎቱንም፡ጥቅም፡ለሌሎች፡ለማስተዋወቅ፡ስለ፡ወደደ፥ ዐዲሱ፡የ"ዐውደ፡ቀለም"፡መርበቢያው፡ሥራውን፡እስኪዠምር፡ድረስ፥ በባለቤቱ፡በአቶ፡ወሌ፡ነጋ፡ፈቃድ፥ መግበሩን፡ማንኛው፡ሰው፡ከመርበቢያችን፡ከ slttunhzb.net፡በነጻ፡ሊቀዳው፡እንደሚችል፡እናስታውቃለን።
የጕዳዩን፡አካኼድ፡ተከታትለን፡በመጪው፡ዕትማችን፡እንዘግባለን፨

Wazéma System•Wazéma Système

© የኢትዮጵያውያን፡ሀገራዊ፡ሥልጡንሕዝባዊ፡አንድነት፡(ኢ.ሀ.ሥ.አ.)፥2008-2014፡ዓ.ም.።